
ግብፅ የናስር ሃይቅ ክምችቷን ስለምትጠቀም በመጀመሪያው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማይደርስባት የሃገሪቱ የውሃ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መሃመድ አልሰበይሂ ተናገሩ፡፡
ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በዚህ ጉዳይ ላይ እያንዳንዱ በሃገሪቱ የሚገኙ ተቋማት የራሳቸው ሚና እንደሚኖራቸው በመግለፅ መንግስት በሃገሪቱ ውስጥ በእያንዷንዷ ጠብታ ውሃ ላይ ቁጥጥር እና ጥበቃ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡
እንዲሁም ግብጽ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማያደርስ መልኩ ኢትዮጵያ የአባይን ውሃ በመጠቀም ልማቷን የማረጋገጥ መብት እንዳላት ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ጋር የነበረው መሰረታዊ አለመግባባትም በድርቅ ወቅት የውሃ አስተዳደሩ በጋራ በማድረጉ ጉዳይ ላይ መሆኑንም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡
ምንጭ፡-አልጀዚራ ቴሌቪዥን